TM Law Firm Accessibility
×
የፌደራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ከባለድርሻ አካላት ጋር የካቲት 26 ቀን 2018 ዓ.ም የምክክር መድረክ አካሄደ፡፡

የፌደራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ከባለድርሻ አካላት ጋር የካቲት 26 ቀን 2018 ዓ.ም የፍትህ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ፣ የከፍተኛ ፍርድ ቤት ም/ፕሬዚዳንት፣ የኢትዮጵያ ን/ዘ/ማ/ም/ቤት ም/ፕሬዚዳንት፣ የአ/አ/ታ/ይ/ኮሚሽን ፕሬዚዳንት በተገኙበት የምክክር መድረክ አካሄደ፡፡ የTM Law Firm አባላትም ተገኝተዋል ፡፡



በውይይት መድረኩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የፍትህ ሚኒስቴር አማካሪና የተጠሪ ተቋማት አስተባባሪ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ፤ ኮሚሽኑ እንደተቋም ከመንግስት የተሰጠውን ተግባርና ኃላፊነት ተግባራዊ ለማድረግና ስራውን በተገቢው ሁኔታ ለመተግበር እና በተቋሙ የሚሰጠው የውሳኔ ጥራት በህግና በአሰራር ወጥ እንዲሆን ለማድረግ ከሚመለከታቸው ባላድርሻ አካላትና የንግዱ ማህበረሰብ ጋር ግብዓት ለማግኘት ምክክር ማድረግ ተገቢ እና አስፈላጊ መሆኑን ገልፀው በቀጣይም ቋሚ በማድረግ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡